ተረትና ምሰሌ
- የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ
- የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች
- የነፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል
- ከአህያ የዋለች ፈረስ ፈስ ተምራ ትገባለች
- ጉልቻ ቢቀያያር ወጥ አያጣፍጥም
- ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት
- አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት መጽሃፍ አጠበች
- ኑሮ ካሉት መቃብርም ይሞቃል
- ኣንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል።
- ኣይጥ ሞቷን ስትሻ የድመት ኣፍንጫ ታሸታለች።
- ላም ያልዋለበት ኩበት ለቀማ።
- ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ።
- ዥብ ከሄደ ውሻ ጮኸ።
- ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል።